Dec 5, 2012

ፕሬዝዳንቱ ለፓትርያሪኩ እና ለዐቃቤ መንበሩ ደብዳቤ ጻፉ?!



ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ
እኒህ ደብዳቤዎች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ጽ/ቤት እንደ ወጡ ተደርጎ በመሰራጨት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ በአድራሻ ለአራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና ለዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የተጻፉ መኾናቸው ይታያል፡፡
ለአራተኛው ፓትርያሪክ የተጻፈው ደብዳቤ የአገር ሽማግሌዎች ለዕርቀ ሰላሙ የሚያደርጉትን ጥረት ጽ/ቤቱ ሙሉ በሙሉ እንደተቀበለው ይገልጻል፡፡ ሽምግልናውንም መነሻ በማድረግ ቅዱስነታቸው÷ ‹‹ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ ተቀብለው በቅዱስነታቸው የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ይዘው(አስከትለው) ወደ አገርዎትና ወደ ቤተ ክርስቲያንዎት እንዲገቡ›› በማለት ይጠይቃል፡፡
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ለዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የተጻፈው ደብዳቤ ደግሞ የቅዱስነታቸው ወደ መንበር መመለስና የሌሎችም ብፁዓን አባቶች ወደ አገር ቤት መግባት ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ካለው ፋይዳ አኳያ ቅዱስ ሲኖዶስና ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ አምነውበት ውሳኔ እንዲያሳልፉበት ይጠይቃል፡፡ ይህም በኢንጅነር ጥሩነህ አራጋው በሚመራው የአገር ሽማግሌዎች ቡድንና በመገናኛ ብዙኀን የተደገፈ መኾኑን ያመለክታል፡፡
ዛሬ፣ ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ዳላስ ከተጀመረውና ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለበት የዕርቀ ሰላም ንግግር አንጻር የደብዳቤውን አጠቃላይ መንፈስ ለመቃወም ያዳግታል፡፡ ይኹንና ከአጻጻፉና ከአጠቃላይ ፕሮቶኰሉ አንጻር (ግልባጭ ከተደረገላቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አንዱ ‹‹ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የአገር ውስጥ ጉዳዮች›› የተባለ ሚኒስቴር መኾኑ ይገርማል)ደብዳቤው÷ ዕርቀ ሰላሙ እንዲሳካ የሚሹ ወገኖች የዘየዱት ‹‹መላ›› ከማለት በቀር ፕሬዝዳንታዊ ወይም በእውን ከፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት የወጣ ነው ለማለት በፍጹም አይቻልም፡፡ ለማንኛውም የጡመራ መድረኩ ወዳጆች ከመንበረ ፓትርያሪኩ አካባቢ እንዳገኙት ገልጸው ያደረሱን ደብዳቤዎቹን እነኾ!!!

ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ
ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ
The Pres Letter to the Patriarch 01The President's letter to the Patriarch 02
The President's Letter to the AqabeThe President's Letter to the Aqabe 02
Previous Post
Next Post

0 comments: